ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል!!

“ለ አይ አር ኤስ (IRS) በእጃችን ያለውን ማስረጃ አስረክበን ቤተክርስቲያኑን እናዘጋዋለን! መንግስት እንዲወርሰው እናደርጋለን! በኋላ ለምን እንዲህ አደረጋችሁ እንዳትሉን!” በሚል ርእስ ሰላም ተዋህዶ በሚባለው የማህበረ ቅዱሳን ድረገጽ (ዌብሳይት) ተቀጥላ ብሎግ ላይ የተጻፈ የዘለፋና የማስፈራሪያ ጽሁፍ ሲሆን፤ እውነትም የሚካኤል ጠላቶች የገመዳቸው ጫፍ ላይ መድረሳቸውን ከጽሁፉ በግልጽ መረዳት ይቻላል።

ደራሲው ሲዘግብ ሁለት የሚካኤል ቤተክርስቲያን አባል ከሆኑና የማህበረ ቅዱሳን የቅርብ ወዳጅ ከሆኑ ግለሰቦች ሪፖርቱን ያገኘ መሆኑን ገልጿል። እንዴ? እንዲህ ያሉ ሊቆች፤ ሊቀ ሊቃውንት፤ ከወዴት ተገኙ? አይ ሞኙ! ተላሌ! የትኞቹ አንኮላዎች ናቸው ይህችን የሞኞች የማጭበርበሪያ ዘዴ ሲሞሉህ የከረሙት? ሁለት ያልካቸውስ የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪዎች፤ እነማን ይሆኑ?

ለብሎግህ በጣም ቅርበት ያላቸው ሁለት ቃል አቀባዮችህስ የዘውትር ሪፖርተሮችህ ካህን አሰዳቢዎቹ መስፍን እና የአምሳ አለቃ ተሰማን ነው? ወይስ ከየህ በፊት አንተው ከምታዘጋጀው ከደጀሰላም ድረገጽ ላይ ገልብጠው “ማህበረ ቅዱሳን 501(C)3 ያለው ድርጅት ነው፤ እናዘጋዋለን ሲሉና፤ አብረውህ ሲበዘብዙ ከርመው፤ ይኸ ሌባ ድርጅት ሲሉህ የነበሩትን ቱልቱላዎች ነው? እንዴት ሆኖ!? ነው? ወይስ የሂሳብ ሊቅ ነኝ ባዩ ቡክ ኪፐር እና አጣሪ ነን ባይ ዘመዶቻቸው? ይኼ ምናልባት እውነትነት ያለው ይመስላል።

ምነው አያ ኤፍሬም እሸቴ! በአዲስ አበባ ከተማ ተቀምጠህ የሐመር እና የስምዓጽድቅ ኤዲተር በነበርክ ጌዜ አለማየሁና ግብረአበሮቹ ሙልጭ አድርገው የሚካኤልን ገንዘብ እየዘረፉ በግርማ መታፈሪያ  በኩል ሲያስገቡ የነበረውን አንተስ ታውቀው የል? ነው ወይስ ለዛ ማስረጃ አይቀርብለት መስሎህ? አንተን ብቻም አይምሰልህ! የሚካኤልን ስእለት የበላ በሙሉ በያለበት እያጓራ! እንዳበደች ውሻ እየተቅበዘበዘ ሲሆን፤ ወያኔው እና ለሆዳቸው የቆሙ ግብረአበሮቹ ከቦርድ አንወጣም ብለው ትንንቅ የፈጠሩትንና ሕዝብ አንቅሮ ተፍቶ ከቦርድ የመነቀራቸውን ይዞ፤ በየሰንበቴው ቤት፤ በየዴኒሱና በየስርቻው እየተሰበሰበ የሚዶልተው “ይህን ሁሉ ያመጡብን ያ ዶክተርና አቶ አበራ ስለሆኑ አመጽ አስነስተን፤ ስማቸውን በክለን፤ ሕዝቡን አደናግረን ከቦርድ ማውረድ እና በምትካቸው ፈትለወርቅን መልሰን ማስገባት አለብን” እየተባለ እቦርድ ስብሰባ ላይ ሲቀዳ የኖረው ቴፕ እየተደመጠ ሽለላና ቀረርቶ አንዳንዴም ፉከራ እየተደረገ፤ ባልዋሉበት ጦር ሜዳ የዘረፉት የሕዝብ ገንዘብ ሲቆጠቁጣቸው አካኪ ዘራፍ!! እያሉ የሚቀበሩበትን ጉድጓድ ሲምሱ ይታያሉ።

ይሄ ምንም እንኳን ክርስቲያን ነን እያሉ ባደባባይ አዋጅ ከሚያስነግሩ የሚጠበቅ ቢሆንም፤ የዘረፋ ምንጩ ሲደርቅ፤ በሕዝብ ገንዘብ መንደላቀቅ ሲቀርና፤ እቁቡ ሲጓደል ወደሚቀጥለው ደረጃ በመሸጋገር የተለያዩ ወንጀሎችን ከመፈጸም እንደማይመለሱ ስለሚታወቅ ሕዝቡ በተጠንቀቅ አይኑን ከፍቶ እንዲጠብቅ፤ የሚያየውን ማንኛውንም ወንጀል ለፖሊስ ሪፖርት እንዲያደርግ ጥሪ እያደረግን፤ ወንጀልን አይቶም ሆነ ሰምቶ ሪፖርት አለማድረግ እራሱ እንደወንጀል የሚቆጠርና በህግ የሚያስቀጣ የአሜሪካ ህግ ስለሆነ ሕዝቡ ይህንኑ ተረድቶ በመብቱ እንዲጠቀም ከአደራ ጭምር እናሳስባለን።

ሂሳብ አዋቂ ነኝ ባዩ ቡክ ኪፐር ያዘጋጁት እጅና እግር የሌለውና ብዙ ስሕተቶችን ያዘለ ዓመታዊ የሂሳብ ዘገባ ሰንጠረዥ ከነመሸኛው በአጭበርባሪው ሊቀመንበርና ውሸትን እንደ ልብሰ ተክህኖ በተጎናጸፉት አይን አውጣ የቦርድ ጸሐፊ አማካኝነት ለሕዝብ እንዲሰራጭና ግብርአበሮቻቸውም እስከ ስብሰባው ቀን ድረስ ለስም ማጥፊያ እንደመረጃ እንዲጠቀሙበት ካደረጉ በኋላ የጃንዋሪ አጠቃላይ ስብሰባ ሲደረግ ከላይ እንደተጠቀሰው የወያኔ ተወካዮችና ጥቂት ለሆዳቸው የተገዙ አሽከሮቻቸው ስብሰባውን ሃይጃክ በማድርግ የሂሳብ ሹሙን እና ገንዘብ ያዡን በሐሰት በመወንጀል የመናገር መብታቸውን ገፈው ያዘጋጁትን አጭር ሰንጠረዥ እንኳን ለስብሰባው ተሳታፊዎች እንዳያሳዩም ሆነ ስለሂሳቡ ማብራሪያ እንዳይሰጡ ተደርገዋል።

ይህ ወንጀል የተፈጸመው ዲሞክራሲ በሰፈነበት እና የመናገር መብት በሕግ በተከበረበት አገር ሲሆን የሕግ አስከባሪዎች በተገኙበት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ነው። እነዚህ ግለሰቦች ሕዝቡን በመናቅና እግዚአብሔርን በመድፈር ሕዝብ የመረጣቸውን በአድማና በጉልበት ከቦርድ አውርደው ሕዝብ አንቅሮ የተፋቸውን ደግሞ በቦታቸው ለመተካት እና የእግዚአብሔርን ቤት ለወያኔ መንግስት ለማስረከብ የሸረቡት ሴራና ያስነሱት አመጽ ለሚካኤል ሰይፍ ዳርጓቸዋል። የታወረው አይናቸው ያነጣጠረው ምንም አቅም በሌላቸው በእግዚአብሔር አግልጋዮች ላይ ሲሆን፤ ኃይል ያለው አምላክ ቤቱን እንዴት እንደሚያስከብር የሴራው ተካፋይ የሆነ ሁሉ ድርሻውን እንደየስራው እንደሚያገኘው ሙሉ እምነታችን ነው። የእግዚአብሔርን ኃይል የተፈታተኑ ሁሉ ምን እንደገጠማቸው ማወቅ የሚፈልግ ታሪካቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ተዘርዝሮ ስለሚግኝ በጥሞና ያንብብ።

አንባቢያንን ለማስታወስ ያህል፤ የዚች ያለንባት ሐገር ሕግ፤ እንኳን በሐሰት ለተከሰሰ ቀርቶ ከፍተኛ ወንጀልን ለፈጸመም ቢሆን “innocent until proven guilty” የሚል አመለካከት አለው። ሆኖም ጃንዋሪ 30 ቀን በቤተክርስቲያናችን ውስጥ በወያኔ ተወካዮችና የጥቅም ተካፋዮቻቸው አቀነባባሪነት የተካሄደው ትእይንት ግልጽ ያደረገው ነገር ቢኖር ያሉትንም ሆነ መውጣት የነበረባቸውን የቦርድ አባላት የሚቻለውንም ሆነ የማይቻለውን ሁሉ አድርጎ በነበሩበት ሥልጣን ላይ ለማቆየትና የማህበረ ቅዱሳን አባላትንና ደጋፊዎቻቸውን ለመመለስ እንዲቻል ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የተደረገ ሴራ ነበር።

ከዚህም ሌላ እነዚህን ሁለት የዋህ ግለሰቦች እግዚአብሔርንና ሕዝብን ለማገልገል ሲሉ በቤተክርስቲያን ውስጥ ይፈጸማል ብለው ያልጠበቁትና ያልጠረጠሩት ረመጥ ውስጥ ገብተው ትክክለኛ ሥራ ለመስራት ባደረጉት ጥረት በጥቅም የተሳሰረ ቀለበት ውስጥ ያሉ ሰዎችን በመንካታቸው በሐሰት ተወንጅለው እንዲወገዱ ለማድረግ የተፈጸመ አድማና ሤራ እንደሆነ ነው። በዚያን እለት በነዚህ ሁለት ግለሰቦች ላይ የተደረገው ሁኔታ ከፍተኛ ወንጀል እንደነበረና በሥም ማጥፋትም ሆነ በሕግ ሊያስጠይቅ የሚችል መሆኑን የትእይንቱ አቀነባባሪዎችና ተዋናያኖች የዘነጉት ይመስላል።

እንዲያውም አልፎ ተርፎ የሂሳቡን ጉዳይ የሚያጣሩ ሶስት ሰዎች መመረጥ አለባቸው ተብሎ ስድስት ሰዎች ተጠቁመው ስድስቱም ሂሳቡን እንዲመረምሩ ተመድበዋል። ጠቋሚዎቹ የወያኔ ተጠሪዎች ሲሆኑ፣ ወሳኞቹና መዳቢዎቹ ደግሞ ሃሳዊው ጸሐፊና አለቃው ናቸው። የሚደንቀው ነገር ይህ አጣሪ ቡድን እነማንን የያዘ ነው ቢባል ሁለቱ የሂሳብ ሊቅ የሆነው ቡክ ኪፐር ዘመዶችና አስቀጣሪዎች ሲሆኑ አንዱ ደግሞ ቤተክርስቲያኗን ሲበዘብዝና ሲያዝበዘብዝ የኖረና የከሳሽ ወገን ነው። ከፊሎቹ ደግሞ የወያኔ ዘመዶችና የጥቅም ተካፋዮች ናቸው። እንግዲህ ፍርዱን ለእግዚአብሔርና ለእናንተ እንተወዋለን።

እንግዲህ ይኸው የወያኔ ግሩፕ የወከላቸው ሂሳብ መርማሪዎች ምን ዓላማ ይዘው ይሆን የተነሱት? በጠየቁት ማስረጃ መሠረት ምንም ነገር ማግኘት ስለተሳናቸው ሌላ ተግባር ላይ የተሰማሩ ይመስላል። ምንአልባትም ቤተክርስቲያኑ ያለውን የሂሳብ ሰነድ ሁሉ ሰብስበው ሰላም ተዋህዶ የተባለው ብሎጋቸው እንደጠቆመው ለI.R.S ለመስጠት ይሆን? ለዚህ ነው ሂሳቡ ሐቀኛ በሆነ ኦዲተር ኦዲት መደረግ ይኖርበታል የምንለው። የምርመራቸውን ውጤት እስከምናይ ድረስ ቸኩለናል።

ጥያቄ ለሕዝብ፦
ለመሆኑ ይኼ ሁሉ በገንዘብ ዙሪያ የተሰገሰገ ወንበዴ ለሃያ አመት ሙሉ እንደመዥገር ተጣብቆ በተቀነባበረ ዘዴ ቤተክርስቲያኗን ሲያራቁት እንዴት ዝም ተባለ? ለቤተክርስቲያን ህልውናና ደህንነት የቆመ ክርስቲያን ጠፍቶ? ወይስ በፍርሃት ተውጦ? ይዝረፉት እኔ ምን አገባኝ፤ ምንስ አስጨነቀኝ በማለት ትቶት ወይስ የጥቅም ተካፋይ ስለነበረ?

ይኸ ሁሉስ የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ነኝ ባይ ባለብሎግ የትኛው የቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ ተደብቆ ከርሞ ነው አሁን ከየስርቻው ብቅ ብቅ ያለው? የህዝብ ስብሰባና የቦርድ ምርጫ አይካሄድም እያለ በየሜዳው ሲያናፋ የነበረው ሁሉ፤ ምርጫ ሲካሄድ ደጎሞ፤ ለምን ተደረገ ከማለቱም ሌላ በከፍተኛ የሕዝብ ድምጽ የተመረጡትን አዲስ የቦርድ አባላት እንዳይገቡ ለማድረግ የሞት የሽረቱን ተጋድሏል፤ ለምን? ለእውነት የቆመ ሰው ሕዝብ ከመረጣቸው አገልጋዮች ጎን ቆሞ ለቤተክርስቲያን የሚጠቅም አገልግሎት አይሰጥምን??

ትናንት የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ በመምሰል የሕዝብ ገንዝብ ያለአግባብ በበጎአድራጎት በኩል እየወጣ እየተዘረፈ ነው እያለ ያለቦርድ ፈቃድ ዶኩመንት እያወጣ ለአባላት ሲያድል የነበረው የሂሳብ ሰራተኛ፤ ዛሬ ኢትዮጵያ ሄዶ ተቀብቶ ከመጣ በኋላ ከዘራፊ ጋር አብሮ ተባብሮ፤ ገንዘብ ያዡና ሂሳብ ሹሙ ገንዘብ አጉድለዋል በማለት የራሱን ሂሳብ አላዋቂነት ይሁን ወይም አድር ባይነት አልታወቀም፤ በሕዝብ ፊት ግን በአደባባይ ቆሞ እራሱን አጋልጧል። ይህ ለምን ሆነ? የጤንነት ወይስ የእብደት?

ቤተክርስቲያንን ለአመጸኞች አሳልፎ መስጠት በእግዚአብሔር ዘንድ አስጠያቂ ከመሆኑም ሌላ በምድርም በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን መረዳት የእያንዳንዳችን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ቸልተኝነቱም ያስከተለው ውጤት ይኸው ትናንት ቤተክርስቲያናችንን ከመዝረፍ አልፎ ለመንጠቅ፤ ካልሆነለትም ለማፍረስ በስውር ሲታገለን የነበረው የወያኔና የማህበረ ቅዱሳን ቡድን ከነግብረአበሮቹ ዛሬ ቤተክርስቲያንን በምድራዊ ፍርድ ቤት ከሶ ካንዴም ሁለት ሶስቴ ሞግቷል።

ያም አልሆን ሲል በአደባባይ አይኑን አፍጦና ጥርሱን አግጦ “ሌባ እናት ልጇን አታምንም እንዲሉ” እኛ መዝረፍ ካልቻልን ሌላውን ሰው ሁሉ ሌባ ነው እያልን እርስ በእርሱ አበጣብጠን ካልሆነልን እዛኛው ቤተክርስቲያናችን እንሄዳለን በማለት የራሱን መርማሪ ኮሚሽን አቋቋሞ የሚቀበርበትን ጉድጓድ ሌት ተቀን በመቆፈር ላይ ይገኛል። የዚህ ቡድን የመጨረሻው ውርደቱም “ሰላም ተዋህዶ በመባል በሚታወቀው ብሎጉ ላይ “የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ” በሚል ርእስ “ዘረፋዬን እንድቀጥል ካላረጋችሁኝ ቤተክርስቲያንን ለአይ አር ኤስ ሪፖርት አደርጌ የያዝኩትንም ዶኩመንት አስረክባለሁ” የሚለው ማስፈራሪያው ነው።

አይ አለመታደል! እንዲህ አይነት ከይሲ የሆኑ አሽክላዎች ከምን ውስጥ ይሆን የሚወጡት? ማንንስ ይሆን የሚያስፈራሩት? የመላእክትን አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን? ወይስ ሌብነታቸውን አውቆ አንቅሮ የተፋቸውን ሕዝብ? አይ አር ኤስ እማ ከመጣ በ”money laundering” ሲዘርፉን የከረሙትን እኩያን የተረገሙ ዋልጌዎች ለቃቅሞ ስለሚያስገባልን ቅዱስ ሚካኤል ገላገለን ነበር።

በተረፈ የተሰወረውን ሁሉ የሚያውቅ፤ የሰውን ሃሳብና ተንኮል እስከአጥንቱ የሚመረምር፤ ሁሉን ማድረግ የሚችል፤ ለሁሉም እንደስራው የሚከፍለው ኃያሉ አምላካችን ሰላምንና ፍቅርን እንዲያመጣልን፤ የዘራፊዎችንና የበዝባዦችን መረብ እንዲበጣጥስልን፤ ሰይጣንን ከሚካኤል ቅጥር እንዲያርቅልን፤ ለቤተክርስቲያን ጠላቶች ልብ እንዲሰጥልን፤ በንጹህ ልብ የሚያገለግሉትን ደግሞ እንዲባርክልን ጠንክረን እንጸልይ!! የነገሩትን የማይረሳ፤ የለመኑትን የማይነሳ አምላካችን የልባችንን ይሙላልን!! አሜን!!

ማቴዎስ 21:22 እምነት ካላችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ።

ማርቆስ 11:24 ስለዚህ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ እንደተቀበላችሁት አድርጋችሁ ብታምኑ ይሆንላችኋል።

ሉቃስ 11:9 ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ በርንም አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤ ምክንያቱም የሚለምን ሁሉ ይቀበላል፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ በር ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል።

ትንቢተ ኤርሚያስ 33:3 ወደኔ ጩኽ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና የማይመረመር ነገር እገልጥልሃለሁ።

ወስብሀት ለእግዚአብሔር!!

No comments:

Post a Comment