ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል!!

“ለ አይ አር ኤስ (IRS) በእጃችን ያለውን ማስረጃ አስረክበን ቤተክርስቲያኑን እናዘጋዋለን! መንግስት እንዲወርሰው እናደርጋለን! በኋላ ለምን እንዲህ አደረጋችሁ እንዳትሉን!” በሚል ርእስ ሰላም ተዋህዶ በሚባለው የማህበረ ቅዱሳን ድረገጽ (ዌብሳይት) ተቀጥላ ብሎግ ላይ የተጻፈ የዘለፋና የማስፈራሪያ ጽሁፍ ሲሆን፤ እውነትም የሚካኤል ጠላቶች የገመዳቸው ጫፍ ላይ መድረሳቸውን ከጽሁፉ በግልጽ መረዳት ይቻላል።

ደራሲው ሲዘግብ ሁለት የሚካኤል ቤተክርስቲያን አባል ከሆኑና የማህበረ ቅዱሳን የቅርብ ወዳጅ ከሆኑ ግለሰቦች ሪፖርቱን ያገኘ መሆኑን ገልጿል። እንዴ? እንዲህ ያሉ ሊቆች፤ ሊቀ ሊቃውንት፤ ከወዴት ተገኙ? አይ ሞኙ! ተላሌ! የትኞቹ አንኮላዎች ናቸው ይህችን የሞኞች የማጭበርበሪያ ዘዴ ሲሞሉህ የከረሙት? ሁለት ያልካቸውስ የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪዎች፤ እነማን ይሆኑ?
ጭቃን አድርቆ ተሻሻለ ማለት ዝናብ እስቲዘንብ ድረስ ነው።
ሰላም ተዋህዶ ለህዝብ የተቆረቆረ መስሎ ሰሞኑን ታይቶ ነበር። እኛም እውነት ለመልካም ተግባርና ቤተ ክርስቲያንና ምእመኑን ለማፋቀር የቆመ መስሎን ማመስገን ጀምረን ነበር! ለካስ መልሶ ጭቃ ለመሆን የሚጠብቀው ዝናብ ነበር።

የደጀሰላም ድረገጽ፤ የሐመር እና የስምአጽድቅ ኤዲተር የሆነው በዲሲ ከተማ በግዞት ላይ የሚገኘው የማህበረ ሰይጣን ባልደረባ እና የሚካኤል ሰይፍ የሚያስልፈልፋቸውና የሚያክለፈልፋቸው እኩያን አሳሳቾች እብዙ ውሸት መሀል ትንሽ እውነት በመደብለቅ ሰላምተዋህዶ የሚል ብሎግ ከፍተው ህዝብን ለማሳሳት የሚያደርጉት ጥረት እርቃኑን ስለወጣ አዚማቸው አልይዝ ብሎ ውርደታቸውን እየተጎናጸፉ ይገኛሉ።

የከሳሾች ብሎግ ደግሞ መረዋመታ የሚል ስም ተሰጥቶት እንደመዥገር ተጣብቀው የቤተክርስቲያንን ሀብትና ንብረት ለአመታት ሲዘርፉ የኖሩት እነተኮላ፤ በቀለ፤ ነጋሽ፤ መስፍን ወዘተ፤ ከነግብረአበሮቻቸው ዛሬ የቤተክርስቲያን ሃሳቢ በመመሰል የመሸታ ቤት አሉባልታቸውን አፋቸውን ሞልተው ለማውራትና ለመዘገብ በቅተዋል። እነዚህ የአርዮስ ልጆች ለሚካኤል ቤተክርስቲያን ጓዳቸውን የቀድሞ ሊቀመንበር ለመጥቀስ “ለሚጠጡት ሻይና ለሚበሉት ዳቦ ያህል እንኳን ስሙኒ የማይሰጡ” ሲሆኑ አባል ላልሆኑለት ቤተክርስቲያን አሳቢ በመምሰል እንዳይዘርፉ ያስቆሟቸውን ሁሉ በመወንጀልና ስም በመስጠት ይኮንናሉ። የነዚህን ሌቦች ተግባር በዝርዝር የሚያውቁት የሚካኤል ቤተክርስቲያን አባላትም አንቅረው አክ እንትፍ ብለዋቸዋል።