ትእግስት ፍርሃት እንዳልሆነ ያልተረዳ ህዝብ አወዳደቁ የከፋ ይሆናል!!
 የተከበራችሁ የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል አባላት ሆይ!!

የዚህችን ቤተክርስቲያን ጠላቶች ሴራና እኩይ አላማ ከነተግባራቸው በግልጽ ሕዝቡ እንዲያውቅ ለማድረግ ስናስብ ይፋ የሚወጡበትን እና እርቃናቸውን የሚቀሩበትን ወቅት በራሳቸው ጥያቄ ስላመጡት ለሕዝቡ ማሳወቅ ግዴታ ሆኖ አግኝተነዋል። እስከመቼ ተለባብሰው እሹሩሩ እየተባሉ ይኖራሉ? ሕግ በሌለበት አገር ወንጀል ሲፈጽሙ ኖረው፤ ከዛ አምልጠው እዚህ ሕግ ያለበት አገር መጥተው ደግሞ የሚያውቀን የለም በሚል በየቤተክርስቲያኑ መሽገው ኖሩ።

የወንጀለኛው ቁጥር እየጨመረ በሄደ ቁጥር በሽታቸው እያገረሸ ስለመጣ የተለመደውን ተግባራቸውን በእግዚአብሔር ቤት መለማመድ ቀጠሉ። ሃይ የሚላቸውም ስለጠፋ ጎለበቱ። ጠያቂ ሲነሳም የሌለውን ታሪክ ሰጥተው አዋርደውና አበሻቅጠው ያባርሩታል። ይኸም ድርጊት ያለቁጥጥር የወንጀል መረባቸውን እንዲዘረጉና ተዝናንተው ይህችን ቤተክርስቲያን እንደመዥገር ተጣብቀው ደሟን እንዲመጡ እድል ሰጥቷቸዋል። ሆኖም በማንአለብኝነት ስለታበዩ ጥጋቡ ገፈተራቸውና ሕዝቡን ከመናቅ አልፈው እግዚአብሔርን መዳፈር ጀመሩ። ስለዚህም ነው ጉዳቸው የአደባባይ ምስጢር እየሆነ የመጣው። የእግዚአብሔርን ቤት ስላረከሱና ሰይጣናዊ ተግባራቸውን ሃይማኖተኛ በመምሰል በመቅደስ ሳይቀር በመተግበር በእግዚአብሔር መንፈስ ላይ ስለቀለዱ፤ ስሙን በከንቱ ከሚጠሩት ከሰራዊት ጌታ የእጃቸውን መቀበያው ወቅት ተቃረበ። ታድያ ከእግዚአብሔር መደበቅ ይቻል ይሆን?