ትእግስት ፍርሃት እንዳልሆነ ያልተረዳ ህዝብ አወዳደቁ የከፋ ይሆናል!!
 የተከበራችሁ የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል አባላት ሆይ!!

የዚህችን ቤተክርስቲያን ጠላቶች ሴራና እኩይ አላማ ከነተግባራቸው በግልጽ ሕዝቡ እንዲያውቅ ለማድረግ ስናስብ ይፋ የሚወጡበትን እና እርቃናቸውን የሚቀሩበትን ወቅት በራሳቸው ጥያቄ ስላመጡት ለሕዝቡ ማሳወቅ ግዴታ ሆኖ አግኝተነዋል። እስከመቼ ተለባብሰው እሹሩሩ እየተባሉ ይኖራሉ? ሕግ በሌለበት አገር ወንጀል ሲፈጽሙ ኖረው፤ ከዛ አምልጠው እዚህ ሕግ ያለበት አገር መጥተው ደግሞ የሚያውቀን የለም በሚል በየቤተክርስቲያኑ መሽገው ኖሩ።

የወንጀለኛው ቁጥር እየጨመረ በሄደ ቁጥር በሽታቸው እያገረሸ ስለመጣ የተለመደውን ተግባራቸውን በእግዚአብሔር ቤት መለማመድ ቀጠሉ። ሃይ የሚላቸውም ስለጠፋ ጎለበቱ። ጠያቂ ሲነሳም የሌለውን ታሪክ ሰጥተው አዋርደውና አበሻቅጠው ያባርሩታል። ይኸም ድርጊት ያለቁጥጥር የወንጀል መረባቸውን እንዲዘረጉና ተዝናንተው ይህችን ቤተክርስቲያን እንደመዥገር ተጣብቀው ደሟን እንዲመጡ እድል ሰጥቷቸዋል። ሆኖም በማንአለብኝነት ስለታበዩ ጥጋቡ ገፈተራቸውና ሕዝቡን ከመናቅ አልፈው እግዚአብሔርን መዳፈር ጀመሩ። ስለዚህም ነው ጉዳቸው የአደባባይ ምስጢር እየሆነ የመጣው። የእግዚአብሔርን ቤት ስላረከሱና ሰይጣናዊ ተግባራቸውን ሃይማኖተኛ በመምሰል በመቅደስ ሳይቀር በመተግበር በእግዚአብሔር መንፈስ ላይ ስለቀለዱ፤ ስሙን በከንቱ ከሚጠሩት ከሰራዊት ጌታ የእጃቸውን መቀበያው ወቅት ተቃረበ። ታድያ ከእግዚአብሔር መደበቅ ይቻል ይሆን?

ሕዝቡንስ እንደበግ ስትነዱ፤ ገንዘቡን ስትዘርፉ፤ ቤቱን ስታፈርሱ፤ ስሙን ስታጎድፉ ቅር ሳይላችሁ ተኩራርታችሁ ኖራችሁ። ዛሬ ታዲያ በእናነተው እጅ የሞተው ቤተሰብም፤ የቆሰለውም፤ ያበደውም፤ የተመረዘውም፤ ሁሉም ከያለበት ወጥቶ ቀንም ሆነ ሌሊት ከየገባችሁበት ጉድጓድ እየፈለፈለ ሊያወጣችሁ ዝግጁ ነው። እናንተስ ተዘጋጅታችኋል??

“አላርፍ ያለች ጣት ኩስ ጠንቁላ ትወጣለች” እንደሚባለው እናንተ ያላፈራችሁበትን የሌብነትና የወንጀል ህይወት ሕዝቡ እስከዛሬ ሸፍኖ ከነገ ዛሬ ይሻላችኋል በማለት ቢታገሳችሁ የፈራችሁ ስለመሰላችሁና በየሰንበቴው ቤት ከምታደርጉት ሀሜትና በቤተክርስቲያን ውስጥ ከምታደርጉት ጸያፍ የሆነ የአፍ እላፊ አልፋችሁ የንጹሀን ግለሰቦችን ስም ለማጉደፍ ሰይጣናዊ የሃሰት መርዛችሁን በድረገጽ መርጨት ጀመራችኋል። እስከ አሁን ድረስ ማንነታችሁን እያወቀ ገመናችሁን ሸፍኖ የተሸከማችሁን ህዝብ በአለም መድረክ በሀሰት ስሙን ማጥፋት ወግ ከመሰላችሁ የየአንዳንዳችሁን ማንነትና የተዝጎረጎረ ታሪካችሁን ለአለም መድረክ ማውጣት አይገድም። የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ እንዳላችሁት በእንቁላሏ ጊዜ ብናስቆማችሁ ኑሮ ከእጅ ሌብነት ወደአፍ ሌብነት ባልተሸጋገራችሁ ነበር። ፈርንጅ ሲተርት “ውሸትን መልሰህ መልሰህ ከተናገርክ እውነት ይመስላል” እንደሚለው፤ ሃሳዊ መሲሆች ፈጥራችሁ የምትጽፉትን ክርፋት፤ በሰፈሩት ቁና መሰፈር አለና፤ ቅመሱት!

ለመሆኑ! በሕዝብ ገንዘብ የተቀጠረው ሊቅ ነኝ ባይ እና እራሱን የቤተክርስቲያናችን አለቃ አድርጎ የሾመው የቦርድ ቅልብ በደጀሰላም ቆሞ፤ ሕዝብ የሚጠይቃቸውን አስተማሪዎች መናፍቃን ናቸው በማለት በስልጣኑ እያገደ በምትካቸው የማህበረ ቅዱሳን አባላትን በቤተክርቲያንና በሕዝብ ገንዝብ ሲያግዝ፤ ለምን? የሚል ጥያቄም ሲቀርብለት “ምእመናኑ ምን አገባው? እኛ ያቀረብንለትን መቀበል ነው እንጂ፤ ይኸን አምጡ፤ ያን አታምጡ የማለት መብት የለውም ሲልና፤ እናቶቻችንን፤ እህቶቻችንን፤ ሚስቶቻችንን፤ ሲሰድብ፤ ምን ተደረገ? ምኑ ተነካ? እንዳንበሳ አገሳብን እንጂ!! የወዳጁን የአለማየሁን መርሆ በመከተል “ተወው እባክህ! ይኸን መሀይም ቦርድ! ልክ እናገባዋለን። እኔ በምነግራቸው መሠረት ቢሰሩ ይሻላቸዋል” በማለት ደሰኮረ እንጂ።

በሳምንት አንድ ቀን እየሰራ፤ አፉን ሞልቶ፤ሥራ በዝቶብኛል፤ ደሞዝም አንሶኛል፤ የሶስት ሰው ሥራ ስለምሰራ ደሞዙ በዛው ልክ ሊከፈለኝ ይገባል! ለምሳሌ፡ የርእሰ ደብርን መሪጌታነት፤ የመላእከ ሰላም ሰብስቤን የሃይማኖት ትምህርት፤ የራሴን ወረብና ቅዳሴ በመደረብ እሰራለሁ ሲል “አርፈህ ተቀመጥ! አለበለዚያ መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ!” የሚለው በማጣቱ እንደተዋጊ በሬ አይኑን አጉርጦ፤ ቀንዱን አሹሎ፤ መስቀሉን ጥሎ፤ መሬቱን እየጫረ ማንን ልውጋ? ወይ በሙሉ ልውጋቸውና ቤተክርስቲያኔን ተረክቤ እንደፈለግሁ ልፈንጭባት! የሚል የማይነቃበት ቅዠት ውስጥ ገብቶ እየዳከረ ይገኛል። ማን? እኮ ማን? ይቀስቅሰው? ወዳጆቹና ግብረ አበሮቹ የቦርድ ሊቀመንበርና ጸሐፊ ወይስ የማህበረ ሰይጣን ተውሳከ ደናቁርት?

አንጋፋ የሆኑትንና ሌት ተቀን አመመኝ፤ ደከመኝ ሳይሉ አንድ ቀን ስንኳ ሳያሰልሱ ቤተክርስቲያንዋን ቀጥ አድርገው የሚያገለግሉትን አባት በመቅደስ ውስጥ ለመደብደብ መቋሚያና መስቀል እያፈራረቀ ሲጋበዝ በወዳጁ የማህበረ ሰይጣን ወኪል ገላጋይነት እኚህ አባት ከዚህ ኮርማ የጳውሎስ ካድሬ ዱላ ሊድኑ ችለዋል። ከዛም ቅዳሴው እንዳይተጓጎል በማለት ይቅር ተባብለው ቅዳሴው በስነስርአቱ ተጠናቋል። ነገር ግን ክስ እንዳይመጣና ጉዱም እንዳይወጣ እኝህን አባት በማስፈራራት ወንጀሉ ተሸፋፍኖ ሳይታወቅ እንዲቀር ለማድረግ በእሱና በእንደራሴዎች ብዙ ጥረት ተደርጓል። በኋላም በሕዝብ ጥያቄ እቦርድ ዘንድ ቀርቦ ቢጠየቅ ከመካዱም ሌላ እንዲህ ካደርኩማ በፖሊስ ልከሰስ ይገባኝ ነበር በማለት አላግጧል። ህዝብን ይወክላሉ ተብለው እቦርድ የተሰገሰጉት የወያኔ ቅጥረኞችም ምን ማስርጃ አለ? ሽማግሌው እንደሆኑስ ሊደባደቡ የሞከሩት? እሳቸው ከሰው ጋር ተስማምተው መስራት አይችሉም በማለት ከህዝቡ የመጣውን ጥያቄ በፌዝ እንደዘጉት የዜና ምንጮች ዘግበዋል። እነዚሁ የቦርድ አባላት ከዚህ ቀደም እኒህኑ አባት ከስራ እናባርራለን ብለው ሲሯሯጡ በቂ ድምጽ ባለማግኘታቸው ሳይሳካላቸው መቅረቱ ይታወሳል።

“በኋላ የመጣ አይን አወጣ እንዲሉ” ጭራሽ የጥጋቡ ጥጋብ ከከሳሾቻችንና ከግብረአበሮቻቸው ጋር በማበር ያልደከመበትን ቤተክርስቲያን ነጥቆ ለአቦይ ጳውሎስ ለማስረከብ፤ ባይሆነለት ደግሞ ያገኘውን ዘርፎ ጅሪውን አስከትሎ የራሱን የተሀድሶ ቤተክርስቲያን ለመክፈት ከፍተኛ ትግል በማካሄድ ላይ ይገኛል። ይህ የሃይማኖት አባት ነው ለማለት የሚሰቀጥጠን ግለሰብ ዝጉርጉር የሆነ የህይወት ታሪክ ያለው ሲሆን በአጭር በአጭሩ በማስረጃ አስደግፈን በሚቀጥሉት ሳምንታት በኦድዮም፤ በቪዲዮም፤ በጽሁፍም እንተርክላችኋለን እስከዛው በውጭ እንቅስቃሴውን፤ መውጣት መግባቱን፤ ዎኩን፤ ጆጉን፤ ወዘተ… በቤተክርስቲያን ውስጥ ደግሞ አረማመዱንና፤ የክህነት ስርአት መከተሉን፤ አገልጋይ ነው ወይስ ተገልጋይ? ደሞዝተኛ ነው ወይስ ሁሌ እንደሚነግረን ሃዋርያ? መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን የሚያምን ከሆነ፤ ይገልጠዋል? ወይስ? ሌላም ሌላም የአደግንባቸውን የቤተክርስቲያን ስርአቶች መከተሉን በጥሞና ተከታተሉ።

በተለይም ዘወትር አርብ በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ስም የሚያስተላልፈውን ፕሮፓጋንዳ እና እሁድ ደግሞ ከቅዳሴ መልስ በደጀ ሰላም የቤተክርስቲያናችንን ሰላምና ደህንነት ከሚያደፈርሱና ለማፍረስም ከቅዱስ ሚካኤል ጋር ከሚታገሉ አክራሪ ወያኔያውያንና አስመሳይ ክርስቲያኖች ጋር የሚደረገውን ድራማ፤ እንዲሁም የገንዘብ መዋጮ እና የሸቀጥ ንግድ ልብ ብላችሁ በጥሞና ተከታተሉ። በተረፈ ቤተክርስቲያናችን የቻለችውንና አቅፋ የያዘችውን ጉድ እንደየአስፈላጊነቱ ቴፑን እየተረተርን በቅደም ተከተል ከነማስረጃው እንዘግባለን። “ጅብ የማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ” እንደተባለው አሜርካን አገር ስለገባን ታሪካችን ተፋቀ ማለት ስላልሆነ፤ እስቲ ቤተክርስቲያናችንን ያስተዳድሩ ብለን የመረጥናቸው ግለሰቦች እነማን ናችው እናውቃቸዋልንን? ታሪካቸውስ ምን ይመስላል? ብለን በመዳሰስ አሉባልታ ሳይሆን በሀቅ ላይ የተመሰረተ ታሪካዊ ዘገባ እናቀርባለን። ይቀጥላል….
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

No comments:

Post a Comment